Tuesday, November 20, 2012

ትኩሳት





ትኩስ ወጣትነት፣   

ካልተጠቀሙበት፤

አይጣል ነው ቁጭቱ፣

ሲዝል ትኩሳቱ።

ራስ አሉላ አባ ነጋ


ከአሥመራ ወደ ምፅዋ ለሚወርድ መንገደኛ ምፅዋ ከመድረሱ ሃያ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው፥ ተድአሊ የተባለችውን ቀበሌ ያገኛል። ገና ከጊንዳዕ በታች የሚገኘውን ገደላ ገደል ወርዶ የዳማስን ሜዳ እንዳለፈ የሚጋረፈው የቆላ ሐሩር ይቀበለዋል። …ከሜድትራኒያን አከባቢ የሚነሣው የክረምት ጊዜ በቀይ ባሕር አካባቢ ያሉትን አገሮች ከልሎ በሚወስድበት ወቅት ቃጠሎውና ደረቁ አከባቢ ወደ ለምለምነት ስለሚለወጥ ከጊንዳዕ ጀምሮ እስከ ምፅዋ ያለው ወረዳም ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ የሚታይበት ውበት፥ የሚገኝበት የመሬት ፍሬና የአየር ለውጥ የማይጠገብ ነው።ራስ አሉላም ከጊንዳዕ ወደ ሰሐጢ የወረዱት በጥር አጋማሽ ላይ ነበር። የአየሩ ጠባይ አልፎ አልፎ ዝናብ የሚጥል መሬቱ በልምላሜ የተሸፈነ ነበር። …


ራስ አሉላ፥ በተፈጥሮአቸው ከወረሱት ጸጋ የጦር ስልት ሲያወጡ ወይም ጦርነት ለመግጠም ሲያስቡ የአየር ጠባይንም በቅድሚያ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ነው። ሠራዊታቸው በሐሩር፥ በጨለማ፥ በወባ፥ በኃይለኛ ዝናብ ጎርፍና ጉም እንዳይጠመድባቸው እጅግ ይጠነቀቁ ነበር። ……ራስ አሉላ ከንጋቱ ላይ ሰሐጢ አጠገብ ደርሰው የወታደራቸውን አሰላለፍ በዝርዝር ተመለከቱ። … ፀሐይ ስትወጣ ከጀርባቸው እንድትሆን አደረጉና ጦርነቱን ጀመሩ። … የመድፍና የጠመንጃው ተኩስ ቀረና ውጊያ በጨበጣ ሆነ። ራሳቸው ራስ አሉላ ከፈረሳቸው ወርደው እንደ ተራ ወታደር በተድአሊ ወንዝና ዳገት እየዘለሉ ከጠላት ጦር ጋር ተደባለቁ። … ጉራዕ ላይ በግብፅ ኩፊት ላይ በድርቡሹ አንገት ላይ በደም ያጠቡትን ጎራዴያቸውን መዘዙና የጣልያኑ ጦር መከላከያ ለመሥራት ሲጣደፍበት ወደነበረው ቁብታ ወጥተው ለሸለሹት። …


[…አቀንቃኝ…] ኪዳኔ መብራቱም፥


“ጎራው ተማሙቋል መሬት ተደባልቋል፤

ነጩ ክምር ፈርሶ ምስቅልቅሉ ወጥቷል።

…ሚስትህ ምነው ባየች በሰማች እናትህ፤

በአሉላ ጎራዴ ሲበጠስ አንገትህ።

የነማን አገር ነው ብለው ሳይጠይቁ፤

አገር የደፈሩ እነሆ ወደቁ።

ምነው በጠየቁ የግብፅን ወታደር፤

ምነው በጠየቁት የድርቡሽ ወታደር፤

እንደማይደፈር ያባነጋ መንደር።”እያለ አቅራራ።

አሉላ አባ ነጋ | ከማሞ ውድነህ | 1979 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 237-241

Tuesday, May 15, 2012

የሁለቱ ሀያላን ነገስታት ዘር!


....ሳሊምቢኒ ጥቅምት 1 ቀን፣ 1890 በያዘው ማስታወሻ፣ አጤ ምኒልክ ትግራይ በነበሩ ጊዜ የተፈፀመ አንድ ታሪክ አንስቶአል።                  

በዚያን እለት ምሽት አጤ ምኒልክ ትግራይ ላይ ከተከሉት ንጉሳዊ ድንኳናቸው ተቀምጠው የቀጠሯትን አንዲት ሴት እየጠበቁ ነበር። እንደተጠበቀውም ማምሻው ላይ ወይዘሪቷ በሁለት አሽከሮች አጀብ በበቅሎ እየሰገረች ከአጤ ምኒልክ ድንኳን ደረሰች። በአካባቢው ብዙ ግርግር አልነበረም። ጥቁር ካባ የደረበች፣ በአበሻ ቀሚስ የደመቀች፣ ጠይም ረዘም ያለች ወይዘሪት ከበቅሎ እንደወረደች በጥድፊያ ወደ ንጉሱ ድንኳን እንድትዘልቅ ተደረገ። ይህች ሴት አልጣሽ ቴዎድሮስ ትባላለች። የአጤ ቴዎድሮስ ሴት ልጅ ስትሆን፣ የአጤ ምኒልክ ደግሞ የመጀመሪያ ሚስት ነበረች።            

ንጉሱ ባዘዙት መሰረት ሁለቱ የቀድሞ ባልና ሚስት በአንድ ገበታ ላይ ለእራት ቀረቡ።  የታሪክ መፃህፍት በደፈናው፣ “መሶብ ቀረበ” ብቻ ብሎ ይገልፀዋል። ርግጥ ነው ይህ ቃል በቃል በበርካታ በመፃህፍት ተገልፆአል። ሁለቱ የቀድሞ ባልና ሚስት በዚያን ሌሊት አብረው ማደራቸውም ተፅፎአል። የራት ቆይታቸው ረጅም ነበር። ሆኖም ምኒልክና አልጣሽ ራት እየተመገቡ የተጨዋወቱት አልተመዘገበም። እንግዲህ ደራሲ እንደመሆኔ፣ በዚያን ምሽት የተነጋገሩትን የመስማት ችሎታና መብት አለኝ። ታሪክን በማጣቀስ በመሶቡ ዙሪያ በምናብ ላቆያችሁ፣አጤ ምኒልክ እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፣“ጤንነትሽ እንዴት ነው አልጣሽ?”

“እኔማ ምን እሆናለሁ ብለሁ ነው? በእግዚአብሄር ፈቃድ አለሁ። የኛ ነገር እንዲህ መላ ማጣቱ ያንገበግበኛል እንጂ። በተለይ የአለማየሁ ነገር፣ ወንድም እንደሌለው፣ እህት እንደሌለው እንዲህ ሆኖ ሲቀር….”

“ጥሩወርቅ ናት ያጠፋች። ይሂድ ብላ ፈቀደች። ‘አባቱ እንዲማርለት ይፈልግ ነበር’ ብላ ለእንግሊዞቹ ነገረቻቸው። ወላጆቹ ተፈቀዱ ምን ይደረጋል? ሁላችንስ በዚያን ግዜ ምን አቅም ነበረን? አምላክ የፈቀደው ሆኖአል…”

“አልሆነላትም እንጂ ጥሩወርቅ  ልትለየው መች ፈለገች?”
አልጣሽ እንባዋን እያባባሰች ቀጠለች፣ “…የአለማየሁ ነገር ለመሸሻ የእግር እሳት እንደሆነበት አለ። ምንስ ቢሆን ለአንድ ወንድማችን መች እናንስ ነበር? ጊዜ ነው የጣለን። እርስዎስ ቢሆኑ ከኛ ጋር የወንድም ያህል አይደሉም እንዴ? የኔን ይተውት? ምን እንደበደልኩዎት ባለውእም ትተውኝ ሄደዋል። አባቴ ባባትዎ ላይ በፈፀመው ቂም ይዘው ይሆናል…”

“ክፉ አትናገሪ አልጣሽ? የማይሆን ሆኖብኝ ትቼሽ መሄዴን አጥተሽው ነው? መቸ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነበርኩ? ወርቂት አሳልፋ ለቴዎድሮስ ሰጥታ ልታስገድለኝ አልነበር? ምኑን ይዤ አንቺን ይዤ ልጓዝ? የችግር ሆኖ እንጂ ካንቺ የበለጠ ተገኝቶ መች ሆኖ?”

“ቢፈልጉ እንኳ ከተረጋጉ በሁዋላ ‘አልጣሽ የት ደረሰች?’ ብለው በጠየቁ ነበር። እርስዎ ግን ሌላ አገቡ…”

“ይኸው ፈልጌ አገኘሁሽ አይደለም እንዴ? ከልቤ ያልነበርሽ ቢሆን መች እጠራሽ ነበር? ደሞስ ብቻዬን የማደርገው መች ሆኖ? መኳንንቱ አሉ…”

“እሱስ ልክ ብለዋል። ሆድ ቢብሰኝ ነው። ‘ንጉሱ ጠርተውሻል’ ብለው ሲሉኝ አልቅሻለሁ። የልጅነት ትዳራችን እንዳልታመመ አወቅሁ። እንዲያው ልጠይቆትና ከመረሃቤቴዋ ባላባት ልጅ ከባፈና ጋር እንዲህ መጣበቅዎ ለምን ይሆን? ምናምን አስነክታዎታለች ነው የሚባል…”

አጤ ምኒልክ ምላሽ ሳይሰጡ ዝም አሉ፣“እንዲህ ተጣብቀው ሲያበቁ ደግሞ ምነው ሳያነግሷት መቅረትዎ?”“ባፈና ስምንት ልጆች አሏት። ከሷ ጋር መንገስ የማይሆን ነበር” ሲሉ መለሱ።

“ቢሆንም መቸም ይወዷት ነበር። መልኳ እንኳ ምንም የማይወጣላት ዘንፋላ ናት አሉ። በእድሜ ግን እናትዎ ትሆናለች ሰማን። ይህን ስሰማ አለቀስኩ። እኔ ምን ቢጎድለኝ ነው? ምን በድያቸው ነው? ብዬ ልቤ ተሰበረ።”

አሁንም ምኒልክ ምንም ምላሽ አልሰጡም። 

“ባፈና ዙፋንዎን ለመጣል ተንኮል ሰርታ ነበር ሰማን…”

“ሰዎች አሳስተዋት ነው”

“ስለሚወዷት ይሸፋፍኑላታል መቼም። አስነክታዎታለች እንጂ …”
እንደገና ምኒልክ ዝምታን መረጡ፣“ወልዳለዎት ነበር መባሉ እውነት ነው?”

“ልጁ ባጭሩ ተቀጨ እንጂ ወልዳልኝ ነበር…”

“ከጉራጌ ሴት የሚወለድ ኢትዮጵያን ለብዙ ዘመን ይገዛል የሚል ትንቢት ተነግሮ መኳንንቱ ሁሉ ከጉራጌ ሴት ተዋልዷል ይላሉ።” አለች አልጣሽ በጎን አይኗ ንጉሱን እያየች፣

ምኒልክ ፈገግ አሉ። አልጣሽ ቀጠለች፣

“እርሶም ይህን ትንቢት አምነው  ከቶሮ ልጅ ከወለተስላሴ ወልደዋል ሰማን።”

“ልክ ነው። የቶሮ ልጅ ሁለት ወልዳልኛለች…”

ከጥቂት ዝምታ በሁዋላ አልጣሽ ወሬ ቀየረች፣“ጣይቱስ እንዴት ናት?”

“አጋዤ ናት…”

“ልጅ ባለመውለዷ ይሰማት ይሆን?”

“ጣይቱ ብርቱ ናት። ስለልጅ ሳነሳባት  14 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጃችን ነው ትላለች። አምላክ ልጅ ከለከላት…”

“እኔ እወልድሎት አልነበር? ችላ አሉኝ እንጂ”

“መች ችላ አልኩ? ይኸው መጣሽ አይደል? እግዚአብሄር ፈቃዱ ከሆነ አንቺ የምትወልጂው ልጅ ይነግስ ይሆናል…”

በዚያን ሌሊት አጤ ምኒልክና አልጣሽ አብረው ማደራቸውን ጳውሎስ ኞኞ መፅሃፉ ላይ ተርኮታል። እንደታለመውም ወይዘሪት አልጣሽ ከንጉሱ አረገዘች። ‘ከሁለቱ የታላላቅ ነገስታት ዘር የሚወለደው ልጅ ኢትዮጵያን ለዘልአለሙ ይገዛል’ የሚል ትንቢት ከአዲስአበባ ጆሮ ደረሰ። አጤ ምኒልክም ይህን ተስፋ በማድረግ ከመጀመሪያ ሚስታቸው የሚወለደውን ህጻን በናፍቆት ይጠብቁ ጀመር። ህፃኑ ለመወለድ አንድ  ወር ያህል ሲቀረው ከአልጣሽ ወንድም ከመሸሻ የተላኩ ሁለት መልእክተኞች አዲስ አበባ በመምጣት አጤ ምኒልክን ለብቻ ለማነጋገር ጠየቁ። እንደተፈቀደላቸውም ገብተው አሳዛኝ መርዶ ለንጉሱ ነገሩ።

“አልጣሽ አርፋለች” የሚል ነበር።

አልጣሽ ከመውለዷ በፊት በእቴጌ ጣይቱ ትእዛዝ በመርዝ መገደሏን ሳሊምቢኒ ፅፎአል።

---------------------------------------------------------------------------

(በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ትረካ። የታሪክ ምንጭ፡ ፃውሎስ ኞኞ፣ ‘አጤ ቴዎድሮስ’ ገፅ 439 – 440)  

Saturday, May 5, 2012

ውውውው........ውሸትን እንግታ!


የሰው ልጅ ውሸትን ለተለያየ ምክንያትና አላማ ይጠቀምበታል። አብዛኞቻችን ከሰወች በልጦ ለመታየት ስንል እንዋሻለን።ወይ ደግሞ ሰወችን ለመወንጀል

ውሸትን ባስፈለገህ ሰአትና ጊዜ ልትጠቀመው ትችላለህ።ከእውነታ የተሻለ ቦታ ሲኖረው ትመለከትናብዋሽ ያዋጣኛልበሚል ግልፍ ስሜት አስበህበትም ይሁን ሳታስብበት  ትዋሻለህ።ነገር ግን ውሸት ስትገባበት እንጂ ለመውጣት ከባድ ነው።እናም ስትዋሽ እንዴት፣ወዴት፣ከየት፣ለምን የሚሉትን ጥያቄወች ማስተናገድ ያስጠላሀል።የውሸት ወሬህን ሳትጨርስ ህሊናህ መድማት ይጀምራል።ከዚህ በኃላ ብዋሽ ከምላሴ ፀጉር ይነቀልትለዋለህ ለምላስህ። በሌላ ጊዜ እንዲህ አይነት መዘዝ ውስጥ እንዳይከትህ  ለማስጠንቀቅ ያህል።ነገር ግን ለአሁኑ እራስክን ለማረጋጋት ብለህ ምላስክን እየዋሸኸው እንጂ በሌላ ጊዜ መዋሸትህ እንደማይቀር ልብህ ሹክ ይልሀል::ላብህ እየመጣም ቢሆን ወሬህን ትጨርሳልህ።ነገር ግን ላብህ ሊመጣ አይገባም ነበር።መሪህ ሲዋሹ አላየሀቸውም? ፀጉር የለለውን እራሳቸውን ያካሉ አንጂ ላባቸው አይመጣም።እንዲህ አይነቱ ጥበብ የሚመጣው ደግሞ ብዙ ከመዋሸት ነው።

ጋዜጠኞቹንስ አልሰማሀቸውም? አዲስ ጋዜጠኛ ከሆነ ምላሱ ይተሳሰርና ይንተባተባል።ያላየውንአየሁ፣ያልሰማውንሰማሁ ያልተደረገውንተደረገማለት ስለሚከብደው ትንፋሽ ያጥረዋል።ከትንሽ ሳምንታት ብኃላ ጆሮ የሚስብ ጋዜጠኛ ይሆናል። አንጋፋወቹ ያሰለጥኑታል።  የጋዜጠኝነት ሙያ ብለው መዋሸትን ይከትቡታል። ለነገሩ ህዝቡም ጀሮ የሚሰጠው ለውሸት ነው። አንድ ጋዜጠኛ በቀኝ ጎኑ ተነስቶእስኪ ዛሬ እውነት እውነቱን ልናገርብሎበእንትን ክልል እንትን ወረዳ በድርቅ ተመታቢል ጀሮ የሚሰጠው አያገኝም።ታዲያ ይህ ምን አዲስ ነገር አለውብሎ ጀሮ ዳባ ልበስ ይለዋል እንጂ።

ይህን ሁሉ የተንዘባዘብኩት እዚህ ባህር ዳር ውስጥ እኔ በማስተምርበት የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ውስጥ የሚማሩ ሁለት ህፃናት ሲያወሩ የሰማሁት ነገር ስላስደነቀኝ ነው።እንደነዚህ አይነት ውሸታሞች በህይወቴ አጋጥሞኝ አያውቅም።አይደለም የአራተኛ ክፍል ተማሪወች የአራተኛ ክፍል አስተማሪም እንዲህ አይነት ውሸት ይዋሻል ብሎ ማሰብ ይከብዳል።

የማስተምራቸው ስዕል ስለሆነ እያወሩ፣ እየተጫወቱ እንዲማሩ እፈቅድላቸዋለሁ።እናም ትናንትና ተራራ እንዲስሉ አዘዝኳቸውና እየዞርኩ የሚስሉትን ስዕል መቃኘት ጀመርኩ።ታዲያ በዚህ ሰአት ነበር ጀሮ የሚደፍን፣ ጭንቅላት የሚያዞር ውሸት የሰማሁት።

የሁለቱንም ልጆች ቤተሰቦች አውቃቸዋለሁ።የአንዱ አባቱ ግንበኛ ሲሆን ያንዱ ደግሞ አሳ አጥማጅ ነው።

ታዲያ የግንበኛው ልጅ፦አባቴ እኮ በጣም የታወቀና የሚደንቅ መሃንዲስ ነው። ማንኛውንም ነገር መስራት ይችላል።ራስ ዳሽንን ታውቀዋለህ?” ሲል የአሳ አጥማጁን ልጅ ጠየቀው።

አዎ አውቀዋለሁ”  ብሎ መለሰለት።

እሱን የሰራው አባቴ ነው።”  አለው  

የአሳ አጥማጁም  ልጅ አድናቆቱን ገለጸና በተራውየኔም አባት እኮ በጣም ጎበዝ መርከበኛ ነው።ለምሳሌ ሞት ባህርን ታውቀዋለህ?”  ብሎ  ጠየቀው።

አዎ ሲጠራ ሰምቻለሁ።”  አለ የግንበኛው ልጅ።

እየሁልህ እሱን የገደለው አባቴ ነውአለው። 

ይህን ስሰማ ለእናት ኢትዮጵያ አዘንኩላት።ይህን ትውልድ ይዛ እንዴት ነው ጉዞዋን የምትቀጥለው ስል እራሴን ጠየኩ።ይች ሀገራችን በስልጣኔ ፊት መርታ መርታ ደክሞት ወደ ኃላ እንደቀረች ይታወቃል። አሁን  ግን አይደለም  ወደ ኃላ መቅረት መሞቷ የማይቀር ነው።እናም ልጆቻችን በውሸት በሽታ ሳይጠቁብን ቀድመን እውነትን ከፖሊዮ ጋር እናስከትባቸው።

Friday, May 4, 2012

ለሌላም አይደለ…….


ለሌላም አይደለ…….

እንዲህ ተጠግተሽእጅጉን ቀርበሽኝ፤

አይኖቼ ውስጥ ገብተውአይኖችሽ የሚያዩኝ።

ለሌላም አይደለእኔ መች ጠፍቶኝ።

 

እንጆሪ ከንፈርሽየሚንቀጠቀጠው፤

ምላስሽ ተሳስሮየሚርበተበተው።

አለንጋ ጣቶችሽፀጉሬን የሚቆጥሩት፤

ደባብሰው ደባብሰውፊቴን የሚያቀሉት፤

ለሌላም አይደለእንዲህ የሚሆኑት፤

ፈልገው መሆኑንእኔ መች አጣሁት።

 

የልብሽ ምት ፍጥነትእጂግ የሚንረው፤

ሙቀት የሚሰማሽላብሽ የሚመጣው፤

ለሌላም አይደለእኔ እንደሁ አውቃለው፤

መቶ ብር እንዳለህስጠኝ ለማለት ነው።


ይህ ግጥም የተፃፈው ባንዲት ባለቤቷን ብር መጠየቅ በምትፈራ ሚስትና ይህን ፀባዮን በሚያውቅ ባለቤቷ መካከል ነው::

አለ አሉ ስብሃት…….







አለ አሉ ስብሃት……..

ማን ይውረስ ተናገር ያለህን ሃብት ንብረት፤

መሄጃ ቀንህ ፈጥኖአል ደርሶአል ቢሉት፤

አለ አሉ ስብሃት……….

ተናገር እያሉ ከበው ሲያጣድፉት፤

"ምን ትጠብቃላችሁ አሁን ከኔ አንደበት።

የትኛውን ሃብቴን ለማንስ ላወረሰው፤

ስፅፍ ነው የኖርኩት ንብረቴን ስዘራው።

በውቤ በርሀ ጭርንቁስ ቤቶች ውስጥ፤

ካንዶ ጭን ወደ አንዶ ሳድር ስርመጠመጥ።

አልበቃኝ ሲል ደግሞ ካዛንቺስ ወርጄ፤

ጠጥቼ ሰክሬ ጨርቅ እስኳን አብጄ።

ላቤን አንጠፍጥፌ ላቦን ተጋርቼ፤

ታዲያ በነጋታው ቤቴ ውስጥ ገብቼ።

ስፅፍ እውላለው የራሴውን አዳር፤

አንዲትም ሳላስቀር ሳልደብቅ ሳላፍር፤

የለም የተረፈኝ የማወርሰው ነገር፤

ይልቅ ከቻላቹ ዋሉልኝ ቁምነገር፤

ሁለት ቀኖች ስጡኝ በህይወት እዳድር።"

 

ይህ ጹሁፍ የተፃፈው የደራሲ  ስሀበት /እግዚአብሔር ዜና ዕረፍት ከመሰማቱ

አንድ ቀን ቀደም ብሎ መገናኛ ብዙሃኖች ላይ በተሰማው ወሬ መሰረት ነው::

 

ምስጋና ለ……


አልጋ ላይ ስንወጣ፣በስሜት ማእበል፤

ትንፋሽሽ ቁርጥርጥ፣እልም ስልም ሲል፤

በጭኖችሽ መሃል፣ስለፋ ስታገል::

ፀጉርሽ ነው የዛኔ፣አለሁህ የሚለኝ፤

በረታ ግፋ እያለ፣ላቤን 'ሚጠርግልኝ፤

የዛኔ ነው ታዲያ፣ስሜቴ ጫፍ ደርሶ የሚወጣጥረኝ፤

የፀጉርሽ ውበቱ፣ደምቆ የሚታየኝ………

 

ጡቶቺሽ ይምጡብኝ……….

የጥጃ ቀንድ መስለው፣ያጎጠጎጡልኝ፤

በዚያ በጭንቅ ሰአት፤

ልፊያ በበዛበት፣አየር በጠፋበት፤

ግየ ተቃጥየ፣ በስሜሽ ሙቀት::

ጉሮሮየ ደርቆ፣ሊሰነጠቅ ሲያምረው፤

ምን ይውጠኝ ነበር፣ጡትሽን ባልጠባው፤

ደረቴን ሲወጉት፣ሲቆረቁሩኝ ነው፤

ስሜቴ ጫፍ ደርሶ፣ጭኔ የሚረጥበው::

 

ኧረግ ኧረግ ኧረግ…..

ካንተ ያስቀድመኝ፣ብየ ፎክርኩለትን፤

ዋናውን ቁም ነገር፣ረሳሁት ቂጥሽን፤

መች እበቃ ነበር፣ለዚህች ቅዱስ ቀን

ስሜቴን ቀስቅሶ፣ባይፈታተነው፤

ላይ ታች ሲራወጥ፣ሲወድቅ ሲነሳ ባልመለከተው::

አሁንስ ቢሆን የድሃ አልጋየን ሲታገል ሊሰብር፤

ጨዋታውን ሊያደምቅ፣ሲኮትን ሲዳክር::

ማን አለ እንደሱ፣የለፋ የደከመ የተባበረኝ፤

ስሜቴን አጡዞ፣ስሜትሽን ያስረዳኝ፤

ሌላ አዲስ አለም፣እንዳለ ያሳየኝ::

ታዲያ ለዚህ ቂጥሽ፣ለባለውለታየ፤

እንዴት ላመስግነው፣እንደምንስ ብየ::

አልታደልኩም ቅኔ፣ ገጣሚም አይደለሁ፤

ዘፈንም አልችልም፣ ስዕል እጠላለሁ::

ያው የኔ ሙያየ፣ያው እንደምታውቂው፤

ወደ አልጋየ ደሴት፣ወደ ተባረከቺው፤

ሲመጣ በፍቅር፣አዝናናልሻለው::