ለሌላም አይደለ…….
እንዲህ ተጠግተሽ፣እጅጉን ቀርበሽኝ፤
አይኖቼ ውስጥ ገብተው፣አይኖችሽ የሚያዩኝ።
ለሌላም አይደለ፣እኔ መች ጠፍቶኝ።
እንጆሪ ከንፈርሽ፣የሚንቀጠቀጠው፤
ምላስሽ ተሳስሮ፣የሚርበተበተው።
አለንጋ ጣቶችሽ፣ፀጉሬን የሚቆጥሩት፤
ደባብሰው ደባብሰው፣ፊቴን የሚያቀሉት፤
ለሌላም አይደለ፣እንዲህ የሚሆኑት፤
ፈልገው መሆኑን፣እኔ መች አጣሁት።
የልብሽ ምት ፍጥነት፣እጂግ የሚንረው፤
ሙቀት የሚሰማሽ፣ላብሽ የሚመጣው፤
ለሌላም አይደለ፣እኔ እንደሁ አውቃለው፤
መቶ ብር እንዳለህ፣ስጠኝ ለማለት ነው።
ይህ ግጥም የተፃፈው ባንዲት ባለቤቷን ብር መጠየቅ በምትፈራ ሚስትና ይህን ፀባዮን በሚያውቅ ባለቤቷ መካከል ነው::
No comments:
Post a Comment