Friday, May 4, 2012

ለልደትሽ.........


እኔ

 እኔ ማለት…………….ከአድማሱ ጀርባ ያለውን አድማስ ለማየት በእግሮቼ ጥፍሮች ጫፍ ቁሜ ስቃየን የማበዛ ፤ከሰማዩ በላይ ያለውን ሰማይ ለማየት አንጋጥጬ አይኖቼን በፀሀይ ጮራ የማስወጋ፤ የአለምን ክብነት ለማረጋገጥ ስል በዙረት ጉልበቴን የማዝል፤መሄዴን እንጂ ወዴት እንደምሄድ የማላውቅ፤ሰላምን ለማግኘት ስል ጦርነት ውስጥ የምገባ፤ለመታመን ብየ የምዋሽ፤አንድ ለማዳን ሁለት የምገድል፤ፍቅርን ዘርቼ በቀልን የማጭድ፤ያሰብኩት ህልም የሚመስለኝ፣ህልሜ ቅዠት የሚሆንብኝ፤አላማ የለለኝ፣አልሜ የማላውቅ፣አላማየን ማለም ያደረኩ፤ቀስ ብዬ ሳወራ የምጮህ፣ስጮህ እብድ የምመስል፣ሳብድ ጭመት የምሆን፣ ጭምት ስሆን የሞትኩ የሚመስለኝ፤እየሞትኩ የምኖር፣እየኖርኩ የምሞት……………

       ይህ ሁሉ የዚህች ከንቱ አለም ውጤት ነው። ታዲያ ሰው እንዴት ወደዚች ብልሹ አለም መጣሁ ብሎ ይደሰታል። ለመሆኑ በእድሜሽ ላይ አንድ አመት ስትጨምሪ ምን እንደምትጨመሪ ታውቆሻል?

አንድ መቶ ሀሳብ ነው የምትጨምሪው።ሰው ልደቱን ይሚያከብረውስ ለምን  ይመስልሻል? የመሞቻው ቀን እየደረሰ ሰለሆነ ደስ ብሎት መሆኑ ነው።ይህቺን ከንቱ አለም ጥሎ የሚሄድበት ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ሲያስብ ደስታ ይሰመዋል። ሰወችም "እንኳን ደስ አለህ" ይሉታል። በወዳጃቸው ሞት መቃረብ ተደስተው።የዘላለም እረፍትን  ሊያገኝ ስለሆነ ቀንተውብት።

ሰው የሚሞተውስ ለምን ይመስልሻል? አድሜ በጨመረ ቁጥር ሀሳብ ይጨምራል።ሀሳብ ደግሞ ጭንቅት ይፈጥራል።ጭንቀት ካለ ችግርና በሽታ ሳትፈልጊያቸው መምጣታቸው አይቀርም። ታዲያ ችግሩ ሲመርሽ እራስሽን ታጠፊያለሽ ወይ ደግሞ በሽታው እራሱ ይገልሻል።  እግዚብሔር ከወደደሽ ወይ ችግር የመትቋቋሚበት ፅናት ይሰጥሻል ወይ ለበሽታ እጇን የማትሰጥ ነብስ ይሰጥሻል።ታዲያ ያኔ የዕድሜ ቱጃር  ይሉሻል።ብዙ አመት በመኖርሽ ሳይሆን  እግዚብሔር ስለወደደሽ እየቀኑብሽ።

እኔ ግን መወለድሽን አልፈልግም::እናም "መልካም ልደት" አልልሽም።ልደት የሞት ዋዜማ ነው።እኔ ደግሞ ሞትሽን አልሻም።እንድሞችብኝ አልፈልግም::ስትሞቺ ከማይ ባትወለጂ ይሻለኛል።

ይህን ሁሉ የምመኝልሽ ስለ…………… ነው::

ይህን ሁሉ የምመኝልሽ አንቺ ማን ነሽ?

አንቺ ማለት…………… ልቤ አክብሮ ያነገሰሽ፤ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የምትታይው፤በትዝታሽ ታስሮ፣ናፍቆትሽ የሚገርፈው፤ፍቅርሽ እንደ በርሀ ውሀ ጥም የሚያቃጥለው፤ከንፈርሽን ሲቀምስ ከነአን የገባ የሚመስለው፤ትንፋሽሽ ህይወት የሚዘራለት፤ የጠጅ ሳር ጠረንሽ ሀሴትን የሚሞላለት ………………ያቺ ሴት አይደለሽም አይደል? አወ አንቺ እሷ አይደለሽም::

አንቺ…………………………..….ነሽ!!

 

No comments:

Post a Comment